tag:blogger.com,1999:blog-2381794331965076077.post7637646732591851088..comments2024-03-05T07:48:19.151-08:00Comments on ጮራ: ምላሽ የሚያሻው የክርስቶስ ጥያቄ - ትወደኛለህን? (ዮሐንስ 21)ጮራhttp://www.blogger.com/profile/10317231175984279644noreply@blogger.comBlogger1125tag:blogger.com,1999:blog-2381794331965076077.post-62606215959156100012016-07-13T07:02:06.562-07:002016-07-13T07:02:06.562-07:00ወገኖቼ ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ልበላችሁ ስሙ!ጌታ ኢየሱስ ከማርያም ተወልዶ ለ3 ዓ...ወገኖቼ ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ልበላችሁ ስሙ!ጌታ ኢየሱስ ከማርያም ተወልዶ ለ3 ዓመት ሲያስተምር ጴንጤ ወይም ኦርቶዶክክስ ወይም ካቶሊክ .... ካልሆናችሁ መንሥተ ሰማይ አትገቡም ብሎ ስለሃይማኖት አሰተምሯል እንዴ?ኧረ እናስተውል?እሱ ያስተማረው ይህን ብታውቁና ብታደርጉ /ዮሐንስ 13፡17/ በማለት፡
1/ አዳም በኃጢአት ምክንያት ከገነት ወጣ = ከእግዜር ተለየ = ሰው ሁሉ /አንተም አንችም እኔም አባም ፓስተርም / ኃጢአትን ሠርተዋልና /ሮሜ 3፡23/ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን /1ኛ ዮሐንስ 1፡10/
2/ የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው /ሮሜ 6፡23/ = ከገነት መውጣት ነው /ዘፍጥረት 3፡24/ = ራቁትነትና በፍርሃት መደበቅ ነው /ዘፍ 3፡10/ = በመርገም ውስጥ መሆን ነው /ዘፍ 3፡15_17
3/ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም /ዕብራውያን 9፡22/ በብሉ ኪዳን ዘመን የእንሳሳት ደም ይፈስ የነበረው ለዚህ ነበር፤ ግን በጥላነት አገለገለ እንጂ ዘለቄታ መፍትሄ አላመጣም።
ስለዚህ የሁላችን ዋና ጥያቄ መሆን ያለበት ከዚህ ኃጢአት ካመጣብን የሞት በሽታ እንዴት መዳንና ከእግዜር ጋር እንታረቅ?መልሱን ከቃሉ አብረን እንይ:
ሀ/ ወንድም ወንድሙን አያድንም፣ ሰውም አያድንም /መዝ 49፡7/
ለ/ እግዚአብሔር ሰውም እንደሌለ አየ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት/ኢሳ 59፡15-17/
ሐ/ ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ /ማቴ 1፡21/ የተመረጠች እናቱ ማርያምም ይህን ተረድታ መድሐኒቴ /ሉቃ 1፡47/አለችው!
መ/ መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና! የለምና! የለምና! የለምና! የለምና! /ሐዋ ሥራ 4፡12/።
ሠ/ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል /ዮሐ 3፡14 እና 15/ ፍቅሩ የገለጠበት መንገድ /3፡6/
ረ/ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም ስላለ /ዕብ 9፡22/ በደሙ ከኃጢያታችን ሊያነጻን /1ኛ ዮሐ 1፡7-9 / ቃል ሥጋ ሆነ /ዮሐ 1፡14/
ስለዚህ ክርስትና በልጁ የመስቀል ሥራ ከሞት መዳን /1ቆሮ 1፡18/ እና የህይዎት ጉዳይ ነው እንጂ /ዮሐ 10፡10/ እና 1ኛ ዮሐ 5፡12/ ሰው ሠራሽ የሆነ የድርጅት ወይም የሃይማኖት ጉዳይ አይደለምና ቆም ብለን ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰማይ የመጣበትንና በመስቀል ላይ ለሁላችን የከፈለውን የህይወት ዋጋ እናስተውል?
ክርስትና በክርስቶስ የደም ዋጋ የተገኘ ሕይወት እንጂ በፍጹም ሃይማኖት አይደለም!!!
በሰማይ ፍቅር የተሸነፍኩና
በጸጋው ቃል ሁለንተና ማንነቴ የተማረኩ
ብቸኛ አዳኝ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ብቻ ብቻ /ሌላ መጨመር በመስቀሉ ሥራ ላይ ብቃት የለኸም ማለት ስለሚሆን / መሆኑ በመጠኑ የገባኝ!ግን ቃሉን በመብላት ወደ ሙላቱ በመገስገስ ላይ ያለሁና ጨለማየ በብርሃኑ የተገፈፈልኝ!!!
ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን!
ያለወንጌል /ሮሜ 1፡1-4/ ክርስቲያን ያስባለንንና
በመርገም ውስጥ እንድንሆን ያደረገን /ገላት 1፡6-9 /
እና እንደ ሳውል/ጳውሎስ /ሐዋ ሥራ 9፡1-9 /
ፎካሪና ገዳይ ሃይማኖተኛ ብቻ ያደረገን ክፉ
የደበተራ መንፈስ በቃሉ ሰይፍ ከሕዝባች ላይ የተሰየፈ ይሁን! አሜን።
የቀደመችው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታማኝ ልጆች አንዱ!
እ ው ነ ቱ ይ ነ ገ ር !!!
Anonymousnoreply@blogger.com