ሃይማኖተ አበው ቀደምት
ካለፈው የቀጠለ
ነገረ ክርስቶስን በምልአት አብራርተዋል
ክርስትና በፍሬምናጦስ አማካይነት በኢትዮጵያ ከተሰበከበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዐፄ ሱስንዮስ ዘመን ድረስ የነበረው የተዋሕዶ ባህለ ትምህርት “ቃልና
ሥጋ በተዋሕዶ
ወልድ ዋሕድ ፩
አካል ፩ ልጅ
ፍጹም አምላክና
ፍጹም ሰው። በተዓቅቦ
፪ ባሕርያት
፪ ግብራት
፪ የባሕርይ
ልደታት ወልደ አብ
በመለኮቱ (በመለኮቱ
የአብ ልጅ) ወልደ
ማርያም በትስብእቱ
(በሰውነቱ የማርያም
ልጅ) አብ ቀባዒ
(ቀቢ)፣ ወልድ
ተቀባዒ (ተቀቢ)፣
መንፈስ ቅዱስ ቅብ
(ቅብዐት)። ሥግው
ቃል (ሥጋ የኾነው
ቃል) በተዋሕዶ
ገንዘብ ባደረገው
በሥጋ ርስት በሥጋ
ባሕርይ መንፈስ
ቅዱስን ከአብ ተቀበሎ
ተቀብቶ፥ በቅባት
መሲሕ ወበኵር
(መሲሕና በኵር)፥
በኵረ ልደት ለኵሉ
ፍጥረት (ከምእመናን ኹሉ በጸጋ ልጅነት የመጀመሪያ ልጅ)፥ ዳግማይ አዳም (ኋለኛው አዳም)፤ ንጉሠ ነገሥት ሊቀ ካህናት፤ ነቢይ ሐዋርያ፣ ላእክ መልአክ (አገልጋይ መልእከተኛ) ኾነ ወይም ተባለ ማለት ነው።” ይላሉ። “ይህ ኹሉ በቅባት የሚሰጥ የሹመትና የግብር ስም” ሲኾን ከመቀባቱ ጋር ተያይዞ መሲሕነቱን አምልቶ አስፍቶ አጕልቶ የሚያሳይ ነው።
ባህለ ትምህርታቸው
ተዋሕዶ ኾኖ ሳለ
በካሮችና ቅብዐቶች
ስማቸው ተቀምቶ
“የጸጋ ልጆች” አንዳንድ
ጊዜም “ሦስት ልደት”
የተሰኙት ለክርስቶስ
ኹለት የባሕርይ
ልደታት፣ አንድ የግብር
ልደት በድምሩ
ሦስት ልደታት
አሉት ብለው ስለሚያምኑና
ስለሚያስተምሩ ነው። ኹለቱ
የባሕርይ ልደታት
የሚባሉትም ወልድ ቅድመ
ዓለም ከአብ ያለ
እናት የተወለደው
ልደትና ድኅረ ዓለም
ከቅድስት ድንግል
ማርያም ያለ አባት
የተወለደው ልደት ነው።
ስለዚህ ወልድ “በአምላክነቱ
የአብ የባሕርይ
ልጅ፥ በሰውነቱ
የማርያም የባሕርይ
ልጅ፥ ፍጹም አምላክና
ፍጹም ሰብእ፥
ወልድ ዋሕድ” ነው።
በመጀመሪያው ልደት ወልድ
የአብ የባሕርይ
ልጅ ነው፤ “ለአብ
ወልድ ዘበአማን
(የባሕርይ ልጅ) በሚባልበት
በአባቱ ባሕርይ
ለማርያም ወልድ ዘበአማን
(የባሕርይ ልጅ) አይባልም፤
ጌታዋ ፈጣሪዋ
እንጂ። እንደዚሁ
ደግሞ ለማርያም
ወልድ ዘበአማን
በሚባልበት በናቱ ባሕርይ
ለአብ ወልድ ዘበአማን
አይባልም፤ ዘበጸጋ
(የጸጋ ልጅ) እንጂ።”
ይላሉ።