Read in PDF
በጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 3 ላይ የቀረበ
መግቢያ፡-
“የጋብቻ ቅንጅት” በተባለው በአንደኛ
ጽሑፋችን በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ተገለጠው የጋብቻ ቅንጅት እግዚአብሔር በሁለት ባልና ሚስት መካከል የሚገኝበት
ቅንጅት ነው፡፡ በቅንጅቱም ባልና ሚስት ፊት ለፊት ተያይተው የልብ መግባባት እንደሚኖራቸው ተመልክተናል፡፡ በአንድ በኩል
የባልና ሚስት እኩልነት እግዚአብሔር እነርሱን በመፍጠሩና በመውደዱ፥ ለክብሩ እንዲኖሩ በዓለም በማስቀመጡ
ተገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል ግን በጋብቻ ውስጥ የሁለቱንም ኀላፊነት ስንመለከት ጐላ ያለ ልዩነት ይታያል፡፡ በመካከላቸው ያለው
የፍቅር ግንኙት እንደ እግዚአብሔር ዕቅድ እንዲሠራ ባልና ሚስት በፈጣሪያቸው ከመጀመሪያ በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን መሠረታዊ
ልዩነት እንዲያስተውሉ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ በጋብቻ ውስጥ ያለው አባወራነት ይህን ልዩነት እንዴት እንደሚያብራራ አሁን ልንመለከት
እንችላለን፡፡
የአባወራነት ሕግ
“የክርስቶስ ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ
ልታውቁ እወዳለሁ፡፡” ይህ የሐዋርያው ጳውሎስ ቃል ሊያስደነግጠን ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ቃል የሚያመለክተን
አባወራነት የተጀመረው በዔድን ገነት ውስጥ ሳይሆን ከዘላለም በሥላሴ ዘንድ ነው፡፡ እኛም ስለ ሥላሴ ስንናገር “አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ” እንላለን እንጂ “ወልድ፥ አብ፥ መንፈስ ቅዱስ” አንልም፡፡ በመለኮታዊ ባሕርይ አንድና
እኩል ሲሆኑ በተግባራቸው የሚገለጥና በአባወራነት የተመሠረተ ቅደም ተከተል አላቸው፡፡ በምድራዊ አባትና ልጅ መካከል ያለውን
ያንጸባርቃል፡፡