Thursday, July 19, 2012

ልዩ ልዩ





በመሠረተ እምነት
ስለ ክርስቶስ መካከለኛነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሰጡትን ምስክርነት በመልክ በመልኩ በማቅረብ አንዳንዶች ዛሬ ቢያስተባብሉትም፥ የክርስቶስ መካከለኛነት ግን በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የታወቀ መሆኑን ያስረዳል፡፡


የዘመን ምስክር
የቀደሙ አባቶቻችን የሠሩትን መልካም ሥራና ያሳዩትን በጎ አርኣያነት የሚዘክረው ይህ ዐምድ፥ የአባ እስጢፋኖስንና የደቂቀ አስጢፋኖስን የተጋድሎ ታሪክ፥ በዚህ ዘመን እየተነሡ ካሉ አከራካሪ ጉዳዮች ጋር በማዋሐድ፥ ስለወንጌልና በምድራችን እንዲመጣ ይፈልጉት ስለነበረው ተሐድሶ ያለፉበትን መንገድ ያስቃኛል፡፡

አለቃ ነቅዐ ጥበብ
በዚህ ዐምድ በደቂቀ እስጢፋኖስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርትና በማኅበረ ቀናዕያን መካከል የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የተደረገውን ጉባኤ የመጨረሻ ዘገባ አቅርቧል፡፡ አለቃ ነቅዐ ጥበብ “እዚህ የቆምሁት ወንጌል የሚያስከፍለውን ዋጋ ለማስታወስ ነው እንጂ፥ በወንጌል ምክንያት የሚነሣውን ተቃውሞ መቀነስ ስለሚቻልበት ሁኔታ አቅጣጫ ለማሳየት አይደለም” ይሉናል፡፡

ወቅታዊ ጕዳይ
ኦርቶዶክስ ማነው? በሚል ርእስ በተከታታይ በሚቀርበው በዚህ ርእስ ማኅበረ ቅዱሳን በአስተምህሮው ኦርቶዶክሳዊ መሆን አለመሆኑን ይፈትሻል፡፡ በዚህ ዕትምም ማኅበሩ ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለው አመለካከት ሲገመገም፥ እግርን ራስ፥ ራስን እግር አድርጎ እንደሚመለከትና ሌሎችንም ነጥቦችን አቅርቧል፡፡

ሌሎችም ጽሑፎች ተካተዋል፡፡

መጽሔቱን በየመንፈሳዊ መዝሙር ቤቶች ያገኙታል፡፡

No comments:

Post a Comment