የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ
በጮራ ቊጥር 5 ላይ የቀረበ
ካለፈው የቀጠለ
በሰሜንም በደቡብም ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ነገዶች የየራሳቸውን አምልኮት ይዘው
እንደ ገቡ ሁሉ እስራኤላውያንም በብሉይ ኪዳን ላይ የተመሠረተውን አምልኮተ እግዚአብሔር ይዘው በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል
ስለ መባሉ ባለፈው ዕትም (ጮራ ቊ. 4) ላይ አስነብበናል፡፡
የአምልኮት መወራረስ የተለመደ ነውና እስራኤላውያንም በጋብቻ፥ በአሰፋፈር፥ በጉርብትና፥
በንግድ ልውውጥና በመሳሰለው አዛማጅ መንገድ ተባባሪና ተጣማሪ ለሆኗቸው ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሀልዎተ እግዚአብሔርን ሳይሰብኩላቸው
ሥርዐተ አምልኮታቸውንም ሳያስተምሯቸው እንዳልቀረ ከማሰብ የሚገታ ምክንያት አይኖርም፡፡