Wednesday, January 23, 2013

ልዩ ልዩ



ስለ ተሐድሶ ጥያቄ አለኝ፤ ሃይማኖት ይታደሳልን?

በየትውልዱ የኖሩና ያለፉ ሰዎች ውቀውም ሆነ ሳያውቁ በዘመን ብዛት የሚፈጥሩት ልብ ወለድ ትምህርት እውነተኛውን የሃይማኖት አካል ያቈሽሸዋል፤ ይሸፍነዋል፤ ይቀብረዋልም፡፡ መቈፈርና የተቀበረውን ማውጣት፥ ቈሻሻውን ማስወገድና የሃይማኖትን ጥራት በእግዚአብሔር ቃል መጠበቅ ግብረ ተሐድሶ ነው፡፡ ለምሳሌ፥ ሰው ሥራ ውሎ ሲገባ፥ ከመኝታው ሲነሣ፥ ቈሻሻ ሲነካው፥ ሲደክመውና ሲያልበው ይታጠባል፡፡ በውሃና በሳሙና ቈሻሻውን አስወግዶ ራሱን ወደ ቀድሞ ንጽሕናው ይመልሰዋል፡፡ የመታጠቡም አስፈላጊነት በተፈጥሮ የታደለውን የአካሉን ቁመናና ቅርጽ    የውስጣዊ ብልቶቹንም ብዛትና አቀማመጥ ለመለወጥ አይደለም፤ ተፈጥሮውን ያበላሻውን ቈሻሻ በማስወገድ ጥንተ ተፈጥሮውን በንጽሕናና በጤንነት ተጠብቆ እንዲኖር ለማድረግ ነው እንጂ፡፡ ከግብረ ተሐድሶ አንዱ ይህን ይመስላል፡፡

(በጮራ ቊጥር 5 ላይ የቀረበ)

1 comment:

  1. what a blessing having this web site .GOD bless you.and Ethiopia

    ReplyDelete