የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(በጮራ ቊጥር 2 ላይ የቀረበ)
ዓለም ፍጥረት ኦሪት ዘፍጥረት 1
እግዚአብሔር የፍጥረትን ታሪክ ለማን እንደ ገለጠ፥ ወይም መጀመሪያ
ማን እንደ ጻፈው በመጽሐፍ ቅዱስ ባይገለጥም ከጥንት የመጣ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ ለእግዚአብሔር ሕዝብም የተሰጠ፥ መሆኑ
ግልጥ ነው፡፡
ይህንን ታሪክ ስናነብ አንዳንድ ነገሮችን መገንዘብ ያስፈልገናል፡፡
ሀ. በእስራኤል ዙሪያ
የነበሩ አረማውያን ፀሓይን፥ ጨረቃንና፥ ሌሎች ብዙ ፍጥረታትን ያመልኩ ስለ ነበር የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ አምላካቸውና ስለ
ፍጥረቱ በትክክል እንዲማሩ አስፈላጊ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ሰዎች ወደ ፀሓይና ጨረቃ በአምልኮት እንዳይመለከቱ ጸሓፊው “ትልቁ
ብርሃን” ና “ትንሹ ብርሃን” እያለ እንዳስገነዘባቸው ይታያል፡፡
ለ. ትምህርቱ
ለሕዝቡ በሚመቻቸው በዚያ ዘመን አገላለጥና ቋንቋ እንጂ አሁን እንዳለው ዘመናዊ ትምህርት አልተሰጠም፡፡
ሐ. እግዚአብሔር ቀን
እየሠራ ሌሊት እያረፈ በሰው ተመስሎአል፡፡
መ. ታሪኩ “ቀን”
ሲል መደበኛውን ኻያ አራት ሰዓት ሊያመለክት ይችላል፤ አንዳንድ ሊቃውንት ግን “ዘመን ነው” ብለው ይተረጒሙታል፡፡ የቀሩት
ደግሞ የታሪክ ማስረጃን ሳይክዱ የደራሲው ዐላማ አንባቢዎች በየቀኑ በተግባራቸውና በጸሎታቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲኖሩ
በሰባት ቀን የተወሰነ ላለመሆኑ በጽሑፉ አቀራረብ ይታያል ይላሉ፡፡ ስለ አንዳንድ ነገር አተረጓጐም ልዩ ልዩ አስተያየት
ቢኖርም ምዕራፉ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ይገልጣልና ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ እንዲጽፉ ይጋበዛሉ፡፡
1.
ከቊጥር
1-3 ስለ እግዚአብሔር ምን ትማራለህ?
2.
በየቀኑ የተፈጠሩትን
ፍጥረት በሥዕል ወይም ስማቸውን በመጻፍ በትክክለኛው ቦታ በሰንጠረዥ ውስጥ አስቀምጥ፡፡
ከእነዚህ የፍጥረት ቅድም ተከተል ስለ
እግዚአብሔር አሠራር ምን ታስታውላለህ?
3.
ለሚከተሉት
ሰባት ሐረጎች ማስረጃዎች የሚገኙባቸውን የጥቅሶች ቊጥሮች ጻፍ፡፡
- እግዚአብሔር ሁሉን ፈጠረ
- እግዚአብሔር ሁሉን በቃሉ ፈጠረ
- እግዚአብሔር ሁሉን በየዐይነቱ ፈጠረ
- እግዚአብሔር ሁሉን መልካም አድርጎ ፈጠረ
- እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረ
- እግዚአብሔር ሰውን የሥራው መደምደሚያ አደረገው
ከዚህ ምዕራፍ ስለ እግዚአብሔር ህላዌ (መኖር) ኀያልነቱ እንዲሁም ዓለምን ለምን እንደ ፈጠረ ምን ትረዳለህ?
No comments:
Post a Comment