Read PDF
(በጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 3 ላይ የቀረበ)
ዓለም ዛሬ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት በታላቅ ሥጋት ላይ ወድቃ ትሸበራለች፡፡ ድርቅና በረሓማነት የዓለምን ሕዝብ ለረኃብና ለበሽታ አጋልጦታል፡፡ ከዓለም ሕዝብ ከፊሉ ያህል በጐርፍ በረኃብ፥ በበሽታ፥ በመሬት መንቀጥቀጥና በዐውሎ ነፋስ ሕይወቱንና ንብረቱን እያጣ ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፤ አንዱ መንግሥት ከሌላው በፖለቲካ፣ በድንበር እየተናቈረ፥ በንግድ ውድድር እየተጐናተለ፥ ጕልበተኛው መንግሥት ደካማውን እያጠቃ ነው፡፡ እንዲያውም የአንዳንድ አገር ሕዝብ እርስ በርሱ በጦርነት ሲተላለቅ ይታያል፡፡ ስለዚህም ነው “ሰላም! ሰላም!” የሚል ድምፅ በዓለማችን ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተጋባው፡፡