Read in PDF
በጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 4 ላይ የቀረበ
ይቅር ባይነት እንማር
ሰዎች የምንባል ሁሉ በልዩ ልዩ አገርና ስፍራ የተወለድን
ከልዩ ልዩ የሰው ዝርያ (ነገድ) የተገኘን እንደ መሆናችን መጠን በቋንቋ በአኗኗር፥ በአመጋገብ፥ በአለባበስ፥ በአስተሳሰብ
በአጠቃላይ በባህል፥ በሙያና በመልክ ቀለም መለያየታችን የታወቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በመካከላችን ከሚታዩት ጥቃቅን ልዩነቶች
ይልቅ ሁላችን አንድ የምንሆንበትና የምንመሳሰልበት ነገር ጒልህ ሆኖ የሚታይ መሆኑን ማስታወስ አለብን፡፡
በተለይ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ አንድነታችንን ለመጠበቅ፥
የተጣለብንን አደራና ዓላማ ያለውን ክርስቲያናዊ አገልግሎታችንን በሚገባ ከግቡ ለማድረስ እንድንችል በብዙ ሜዳዊ ልዩነቶች
መካከል የምንመሳሰልባቸውንና አንድ የሚያደርጉንን ቁም ነገሮች መገንዘብም ማሰላሰልም ያስፈልገናል፡፡