የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
በጮራ ቊጥር 4 ላይ የቀረበ
ኦሪት ዘፍጥረት 3፥1-13
መግቢያ
ሰው
ይህን ምዕራፍ ካልተረዳ ጠቅላላውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ እንደዚሁም የዓለምንና የሰውን ሁኔታ ሊያስተውል አይችልም፤ ስለዚህ
ከማንበብህ በፊት እግዚአብሔር ምስጢሩን እንዲገልጽልህ ጸልይ፡፡
ሰው
እግዚአብሔር ካዘጋጀለት ክብር፥ ጸጋ፥ በረከትና ብፅዕና ወደቀ፡፡ የአዳም ታሪክ የእኛ ታሪክ ነው፡፡ በአዳም ውስጥ ሆነን
(ተቈጥረን) ኀጢአት ሠራን፤ በእርሱ ሞትን (ሮሜ 5፥12፡15፡18፡19)፡፡
ይህም ብቻ ሳይሆን የአባታችንን ስሕተት ተከትለን በሰይጣን እየተሳሳትን በየጊዜው እንወድቃለን፡፡
ምንባቡን
ስታነብ የሚከተሉት ማስታወሻዎች ሊረዱህ ይችላሉ፡፡
ቍ.
1 እባብ
አንቀጹ
እባብ ሰይጣን ነው አይልም፤ ሆኖም ፈተናው ከሰይጣን (ከዲያብሎስ) እንደ ተነሣ ዮሐ. 8፥44፤ ራእ. 12፥9፤ 20፥2 ይገልጻሉ፡፡
ሰይጣን የእግዚአብሔር መልአክና ፍጡር ሲሆን ምን ጊዜ እንደ ወደቀ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም፡፡
ተንኰለኛ
የዕብራይስጥ
ቃል “ዘዴኛ” ወይም “ጮሌ” ማለት ሲሆን፥ ክፋትን አያመለክትም፤ እንግዲህ እባቡ ለሰይጣን ክፋት ምቹ መሣሪያ ሆነ፡፡
ቍ.
3 አትንኩትም፤ ሴቲቱ ይህን ትእዛዝ በእግዚአብሔር ቃል ላይ
ጨመረች (2፥17)፡፡
ቍ. 6 ሴቲቱ ዛፍ … አየች፤ አንዳንዶች እግዚአብሔር ዛፍን ባይፈጥር ኖሮ ሰው አይወድቅም ነበር በማለታቸው የዛፍን ዐላማ
አያስተውሉም፤ ምክንያቱም ዛፍ የሰው መታዘዝና ለእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ መለኪያ በመሆኑ ፈተናው ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ተደረገ፡፡
ሴቲቱ በሐሳብ የወደቀችው የእግዚአብሔርን ቃልና አስተሳሰብ ትታ፥ በራስዋ አስተሳሰብ ስትመራ ነበር፤ በኋላም ሐሳቡ ወደ
አድራጎት በቀላሉ አደረሳት፡፡
ቍ. 7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ አሁን በመልካምና በክፉ መካከል ያለውን ልዩነት ተረዱ፤ ግን እባብ ባሳሰባት ዐይነት
አልነበረም (ቊ. 5)፡፡
የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው፤ እነዚህ ቅጠሎች መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ መወሰዳቸውን አንቀጹ አይገልጽም፡፡
1.
የሰይጣን ተንኰል (ቍ. 1-6)፡፡
በእባብ አቀራረብ አጠያየቅ የሰይጣንን ተንኰል መርምር፡፡
ሀ) የእባቡ ተንኰል በፈተናው ቦታና በሴቲቱ ሁኔታ እንዴት ይታያል?
ለ) በሴቲቱ ላይ ጥርጥር ለመፍጠር ምን አደረገ (1)?
ሐ) ምን ውሸት ተናገረ (4)?
መ) የእግዚአብሔርን ስም እንዴት አጠፋ(5)?
ሠ) መልካም ነገርን ለክፉ ውጤት እንዴት ተጠቀመ (6)?
ረ) ሴቲቱ
የእግዚአብሔርን ቃልና አስተሳሰብ እንድትተውና በራስዋ አስተሳሰብ እንድትመራ ምን አደረገ (1-6)?
ሰ) በእባብ ንግግር ውስጥ
ምን ያህል እውነት ነበር?
ሸ) ምን ያህልስ ሐሰት ነበር?
2.
የሴቲቱ ስሕተት (ቍ. 1-6)፡፡
የእግዚአብሔርን ግልጽ ትእዛዝ ከመተላለፍዋ በፊት ሴቲቱ ስፍራዋንና ሥልጣንዋን፦
ሀ) ከእንስሳት ጋር
ለ) ከባልዋ ጋር
ሐ) ከእግዚአብሔር ቃል ጋር
መ) ከእግዚአብሔር ጋር
ሠ) ከራስዋ ተፈጥሮ ሁኔታ ጋር (1፥28) እንዴት አላከበረችም?
3.
የአዳም ስሕተት
እርሱ ለውድቀት ተጠያቂ ለምን ሆነ (1ጢሞ. 2፥13-14)?
4.
የውድቀት ውጤት (7-13)
ሀ) ከፊተኛው ንጽሕናቸው፥ ክብራቸውና ከራሳቸው ተፈጥሮ
ባሕርይ በምን አኳኋን ተለዩ? (ቊ. 7)
ለ) ከእግዚአብሔር በምን አኳኋን ተለዩ (8-9)?
ሐ) እርስ በእርሳቸው በምን አኳኋን ተለያዩ (10-13)?
5.
የእግዚአብሔር ቸርነት (9-13)፡፡
እግዚአብሔር ንስሓ እንዲገቡ ምን አደረገ?
6. ኀጢአታቸውንና የበደላቸውን ስሜት ለመሸፈን ሲሞክሩ በምን
ዓይነት “የበለስ ቅጠሎች” ይጠቀማሉ?
No comments:
Post a Comment