ካለፈው የቀጠለ
በምን ተስኖት ቤት
ዐድረው ከወጡት ሰዎች መካከል በሌላ አቅጣጫ የሄዱትም እንደዚሁ በተመሳሳይና በሌሎች የወቅቱ ሁኔታ በፈጠራቸው ነጥቦች ላይ ይከራከሩ
ነበር፡፡ ሐሳባቸውን በውይይት እያጠነከሩና እየተስማሙ መጥተው በመጨረሻ በአንዳንድ ነጥብ ላይ ለመግባባት አልቻሉም፡፡ ከብዙ ውይይት
በኋላ ያስቸገሯቸውንና አልታረቅ ያሏቸውን ነጥቦች በሚከተለው ሁኔታ አጠቃለሏቸው፡፡
1. ምን ተስኖት በሰይጣን መንፈስ እንደሚሠራ እናውቃን፤ ከጥንቈላ፣
ከሟርት፣ ከአስማተኛነት ጋር የእግዚአብሔር መንፈስ ግንኙነት የለውምና፥ ለእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርብ የሚገባውን ክብር፣ አምልኮት፣
ስግደትና ዝማሬ የሚቀበለው በምን ተስኖት ያደረ ራሱን የእግዚአብሔር ተገዳዳሪ ያደረገው ሰይጣን ነው፡፡ ታዲያ ሰይጣን በምን ተስኖት
ቤት ሲመለክ የሚያድርበትን ዕለት በየወሩ ለሚካኤልና ለገብርኤል መታሰቢያ በሚከበሩ በዓላት ለምን አደረገው?