Sunday, October 5, 2014

ማስታወቂያ

ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቍጥር 46 ለንባብ በቃ


ርእሰ አንቀጽ፦
“ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን” በሚል ርእስ የቀረበው ርእሰ አንቀጽ ኢየሱስን ማሳየት ትተው ራሳቸውን የሚያሳዩትን አገልጋዮችና ኢየሱስን ማየት ትተው አገልጋዮችን እየተመለከቱ የሚመላለሱትን ሁሉንም ኢየሱስን አሳዩ ወደ ኢየሱስም ተመልከቱ ይላል፡፡

መሠረተ እምነት፦
ኢየሱስ ክርስቶሰ የዐዲስ ኪዳን መካከለኛ በሚል ርእስ ሲቀርብ የነበረው ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻ ክፍል “ኢየሱስ መካከለኛ ነው ማለት ሥጋ ወደሙ መካከለኛ ነው ማለት ነው” የሚለውን የአንዳንዶች አመለካከት በመጽሐፍ ቅዱሰ የመረመረበትን ጽሑፍ አቅርቧል፡፡

ጥያቄዎቻችሁና መልሶቻቸው፦
በዚህ ዐምድ ደግሞ ስለ ጥንተ አብሶ በሊቃውንት መካከል ያለውን ክርክር መሠረት ያደረገ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡

አለቃ ነቅዐ ጥበብ፦
በመዝሙር ላይ እየታዩ ያሉትን ችግሮች በተመለከተ የሰጡትን ትምህርትና በትምህርታቸው ላይ የተደረገውን ውይይት ይዟል፡፡

ታላላቅ መንፈሳውያን ቃላት
ስለክርስቲያናዊ ኅብረት ምንነት መሠረተ ሐሳብና ተመሳሳይ ጕዳዮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አቅርቧል፡፡

ሌሎችም ጽሑፎችን ይዛለች፤ መጽሔቷን እንዲያነቡ ስንጋብዝ በመንፈሳዊና ተሐድሶኣዊ መልእክቶቿ እንደሚጠቀሙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

No comments:

Post a Comment