ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቍጥር 47 ለንባብ በቃ
በዚህ ዕትም፦
- ዕቅበተ እምነት በተሰኘው ዐምድ ለ"መድሎተ ጽድቅ" ክፍል ፩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ምላሹ በ www.chorra.net ቀርቦ የነበረው ተሻሽሎና ዳብሮ ቀርቧል፡፡
- በ "የዘመን ምስክር" ዐምድ የሠራዊተ ክርስቶስ ማኅበርን ታሪክና ለእናት ቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን በጎ አስተዋፅኦ በማውሳት በ "መድሎተ ጽድቅ" እና በሌሎችም ቡድኖች ስለ እነርሱ እየቀረበ ያለውን የተሳሳተ መረጃ ከእውነታው ጋር በማነጻጸር አቅርቧል፡፡
- አለቃ ነቅዐ ጥበብ በሥዕል ዙሪያ ለተነሣ የሁለት ሰዎች ክርክር ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
- በፍካሬ መጻሕፍት ዐምድ በ2ጢሞ. 3፥15-17 ለተጻፈውና ብዙ ጊዜ ስለ አዋልድ መጻሕፍት እንደ ተነገረ ተደርጎ ለሚጠቀሰው ክፍል ዐውዳዊ ፍቺ ይሰጣል፡፡
- "ታላላቅ መንፈሳውያን ቃላት" የተሰኘው ዐምድም ስለ ተሰፋ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልእክት ያቀርባል፡፡
መጽሔቱን በየመንፈሳውያን መጻሕፍት መደብሮች ያገኙታል።
No comments:
Post a Comment