Thursday, January 5, 2012

“እኔ ጐስቋላ ሰው ነኝ . . . ማን ያድነኛል?” (ሮሜ 7፥24)፡፡

Read PDF
(በጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 2 ላይ የቀረበ)

ካለፈው የቀጠለ

መዳንን አጥብቀው የሚሹ በሽተኞች መሆናቸውን የተረዱና የጤና ስንኩልነታቸው ያስከተለባቸው ጕዳትና ውርደት ከልብ የተሰማቸው ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ በብዙ ድካም ያገኙትን መድኀኒት በሚገባ ሊጠቀሙበት ሙሉ ፈቃደኞች  ይሆናሉ (ሉቃ. 5፥31፤ ሐ.ሥ. 16፥30)፡፡ በዚህ ትይዩ እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ያዘጋጀውን መድኀኒት በምስጋና እንቀበለው ዘንድ በቅድሚያ የበሽታችንን ምንነትና ያደረሰብንን ገናም የሚያደርስብንን አስከፊ ውጤት በጥልቀት ልናጠናው ይገባል፡፡

የእግዚብሔር ቊጣና ምክንያት

በኀጢአተኝነትና በዐመፃ ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ እንደሚገለጥ በማስታወቅ ሐዋርያው ጳውሎስ ብርቱ ማስጠንቀቂያ ለሰው ዘር ሁሉ ያስተላልፋል (ሮሜ 118-31)፡፡ ሐዋርያው “ኀጢአተኛነት” ሲል ኀጢአተኛ የሆነውን ሰብኣዊ ባሕርይ ያመለክታል፡፡ እንዲሁም “ዐመፃ” ሲል ኀጢአተኛ ሰው በኀጢአተኛ ባሕርዩ የሚያፈራውን የኀጢአት ፍሬ ይገልጻል፡፡ በዚህ አገላለጽ መሠረት ሰው በሁለት መንገድ ኀጢአት እንደ ተቈጠረበት መረዳት ተችሏል፡፡ ይህም ማለት ኀጢአተኛነትና ኀጢአት ነው፡፡ ሰውን ኀጢአተኛ ባሰኘው ኀጢአተኛ ባሕርዩና ከኀጢአተኛ ባሕርዩ የተነሣ ሰው በሠራው ኀጢአት ላይ መለኮታዊ ቊጣ ሊገለጽ ተገባ፡፡



እንዲህም ከሆነ ሰው ኀጢአትን የሚሠራው በኀጢአተኛ ባሕርዩ ግፊት ምክንያት እንደ ሆነ ይታወቃል (ማቴ. 716-18፤ 12፥34-35)፡፡ ሰው ኀጢአተኛ ተብሎ በተጠራው ኀጢአተኛ ባሕርዩና በኀጢአተኛ ባሕርዩ አስገዳጅነት ባፈራው የኀጢአት ፍሬ /ዐመፃ/ ከእግዚአብሔር ቊጣ እንደማያመልጥ በሐዋርያው ማስጠንቀቂያ ጐልቶ ይነበባል፡፡
የእግዚአብሔር ቊጣ የማይደርስበት የሰው ዘር አለን? ከሁለቱ የሰው ዘር ምንጮች ከአዳምና ከሔዋን የሚወለዱ ሰዎች እየተራቡ ምድርን እንዲሞሏት የእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ነበረ (ዘፍ. 127፡28)፡፡ ስለ ሆነም ከአዳምና ከሔዋን የተወለዱ ልጆችና የልጅ ልጆች እየተራቡ በምድር ላይ እንደ ተስፋፉ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል (ዘፍ. 115-9)፡፡

አብርሃም በእግዚአብሔር ከተጠራና እግዚአብሔርን በማምለክ ራሱን ከወሰነ በኋላ የእርሱ ልጅ ይሥሓቅና የልጅ ልጁ ያዕቆብ የአብርሃምን ዱካ እየተከተሉ የእግዚአብሔርን አምላክነት ብቻ ተቀበሉ፡፡ በኋላ እስራኤል የተባለው የያዕቆብ ልጆችም እስራኤላውያን በመባል ለአምልኮተ እግዚአብሔር ተለዩ፡፡ መናፍስትንና ጣዖታትን ያመልኩ የነበሩ ሌሎች ሕዝቦች ግን አረማውያን በመባል ታወቁ (ዘፍ. 121፤ ዘዳ. 328-11፤ መዝ. 14619-20)፡፡

በሁለት የአምልኮት ክፍሎች የተመደቡት የአዳምና የሔዋን ተወላጆች የእግዚአብሔርን ቊጣ በሚያመጣው ኀጢአተኛነትና በዐመፃ የነበራቸው ልዩነት፡-

-   አረማውያን በተፈጥሮና በኅሊና የሚያውቁትን ሕግ መተላለፋቸው ሲሆን፤
-   እስራኤላውያን ግን በተፈጥሮ በኅሊናና በመጽሐፍ የሚያውቁትን ሕግ በመተላለፍ መበደላቸው ነው ከማለት በቀር ሁለቱም ክፍሎች ምክንያት ሊሰጡ የማይችሉበት ኀጢአተኛነታቸው እና ዐመፃቸው እኩል ከቊጣ በታች አድርጓቸዋል (ሮሜ 211-15)፡፡


ሐሳቡ ሲጠቃለልም የሰው ዘር ሁሉ ኀጢአተኛ ሆኖአልና የእግዚአብሔር ቊጣ ሊወርድበት የተገባ ነው ማለትን የሚከለክል ከሰው ልጆች መካከል ይህ ወይም ያ ይሻላል የሚባል እንደሌለ ሁሉ ዐመፃ ያልተመረተበት የሰውነት ክፍልም አለመኖሩን የእግዚአብሔር ቃል ያረጋግጣል (ዘፍ. 65፡11፡12፤ መዝ. 131-3፤ ኢሳ. 13፡5፡6)፡፡

የክፍሉ መታሰቢያ ጥቅስ፡-

“ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም” (ኢዮ. 144)፡፡
ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment