Read PDF
ይህን ስብከት የሰማ አንድ ወጣት የዚህ ዓለም ሣቅና ጨዋታ ሀብቱንም በመከታተል የሰይጣንን በቄላ እየለቃቀመ ወደ ጥፋት ከሚራመዱት አንዱ እርሱ ራሱ እንደ ነበር አስተውሎ የሚድንበትን መንገድ ለመያዝ ይፈልግ ጀመር፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ድኖ ወደ ሕይወት በሚያደርሰው መንገድ ጌታችንን ለመከተል ከጀመረ በኋላ “በፍጹም ሳልጠፋ እሄድበት በነበረው መንገድ ስላቆመኝ ስለዚያ ስብከት እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ብሎ መሰከረ፡፡ አንተስ?
የሰይጣን ባቄላ
በጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 2 ላይ የቀረበ
የሳባ ታሪኮች ከሚለው መጽሐፍ የተገኘ (የአንድ ሰባኪ ትረካ)
አንድ ቀን እጅግ ብዙ የሆነ አሳማ አንዱን ሰው ተከትሎ ሲጥመለመል አየሁ፡፡ የአሳማ መንጋ ከወደ ኋላ ሆኖ ሲነዱት እንኳ ግራና ቀኝ እያለ ነጂውን ያስቸግራል:: በዚህ ጊዜ ግን ያለ አንዳች ችግር ተቀጣጥሎ ሰውየውን ይከተል ነበር፡፡ እኔም ሁኔታውን ለመረዳት ተከታትዬ ተመለከትሁ፡፡ ሰውየውም እየመራ ከብት ወደሚታረድበት ቄራ ሲደርስ በሩን ከፍቶ የተከተለውን የአሳማ መንጋ አስገብቶ መልሶ ዘጋ፡፡
እኔም ወደ ሰውየው ቀርቤ ያለአንዳች ችግር ይህን የሚያህል የአሳማ መንጋ ወደ ቄራው ውስጥ ልትመራው እንደ ምን ተቻለህ? ብዬ ብጠይቀው ከት ብሎ ስቆ “በብብቴ የያዝኩትን አንድ ከረጢት ባቄላ አላየህም ይሆናል፡፡ አሳማዎቹ ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር ሳንጠባጥብላቸው ወደ መሞቻቸው እንደሚደርሱ ሳያስተውሉ ያንን እየለቃቀሙ ወደሚታረዱበት ቄራ ድንገት ገቡ እንዳይወጡም ዘጋሁባቸው” አለኝ፡፡
ሰባኪው ይህን ያያውንና የሰማውን ከተረከ በኋላ ለአድማጮቹ “እንዲዚሁም ሰይጣን የምትወዷቸውን ነገሮች ደህና አድርጎ ያውቃልና እያንዳንዳችሁን እያታለለ በመንገድ ላይ ባቄላውን እያንጠባጠበ ሲመራችሁ የመጨረሻውን ባቄላ የምትለቅሙበት ሰዓት ፈጥኖ ይመጣባችኋል፤ በዚህ ጊዜ የገሃነም ደጆች ከበስተ ኋላችሁ ይዘጋሉ፤” ብሎ አስረዳ፡፡
No comments:
Post a Comment