Read in PDF
መሠረተ እምነት
የዘመን ምስክር
ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ታላላቅ መንፈሳውያን
ቃላት
ፍካሬ መጻሕፍት
ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 44 ለንባብ በቅቷል

ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ በኋላ እርሱን ተክተው በክህነት እንዲያገለግሉ የሾማቸው ካህናት አሉን? በሚል ርእስ በተዘጋጀው
ጽሑፍ አየሱስን ወክለው የተሾሙ ካህናት አሉ የሚሉ ወገኖችን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይሞግታል፡፡

የዚህ ዕትም የዘመን ምስክር ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ናቸው፡፡ ለአገርና ለወገን ያፈለቋቸው ተራማጅ ሐሳቦች ተዳስሰዋል፡፡
ስለ ሃይማኖት ነጻነት ከተናገሩት መካከል የሚከተለው ይገኛል፥ “… ባገራችን አንድ የድንቊርና
ነገር አለ፡፡ ሃይማኖቱ ተዋሕዶ ያልሆነ ሰው ሁሉ እንደ ርኩስ ይቈጠራል፡፡ ይህም እጅግ ያሥቃል፡፡ አእምሮ የሌለው ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን
ቃል ሳያውቅ የእግዚአብሔር ጠበቃ ሊሆን ይወዳል፡፡”

በዚህ ዐምድ ሥር ለሁለት ጥያቄዎች ምላሸ ተሰጥቷል፡፡ አንደኛው ጥያቄ መልከ ጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነወይ? የሚል ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ “አንዳንድ አጋንንትን እናስወጣለን የሚሉ ሰዎች ግን በኢየሱስ ስም ብቻ ሳይሆን በጻድቃንና
በሰማዕታት ስም እናስወጣለን ይላሉ። በተጨማሪ አጋንንቱ ካደሩበት ሰው ጋር ትግል መግጠም፥ ሰውዮውን በመቊጠሪያ፥ በጧፍ፥ በመስቀል
ወዘተ. መደብደብና የመሳሰሉ ድርጊቶችን ይፈጸማሉ። እነዚህንም ድርጊቶች በሲዲ እያሠራጩ ከክርስትና ትምህርት ውጪ የሆኑ ልምምዶችን
ያስፋፋሉ። እውን እነዚህ ነገሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸውን?”

ስለ ዐዲስ ልደት ምንነት ትምህርት ያገኛሉ፡፡

“ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” ለሚለው ጥቅስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ሌሎችም ጽሑፎች ተካተዋልና ጮራን ያንብቡ፡፡
ሌሎችም እንዲያነቡ በማድረግ መንፈሳዊ አደራዎን ይወጡ፡፡
No comments:
Post a Comment