የመጽሐፍ
ቅዱስ ጠቅላላ ዕውቀት
ከሁሉን
መርምር
በአንዳንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ በብሉይ ኪዳን መጨረሻ ከገጽ 721-1037 በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዞች የማይገኙ መጻሕፍት በመጨመራቸው
ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ያውቃሉን? “ተጨማሪ (ዲዮትሮካኖኒካል) የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት” በሚል የክፍል መጠሪያ የተጨመሩት መጻሕፍት
ዐሥራ ዐምስት ናቸው፡፡
በውሳኔ
የተጨመሩት መጻሕፍት የሚገኙበት ጥራዝ በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ እንደ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ሲቈጠር እነርሱ የሌሉበት ጥራዝ ግን “ጐዶሎ
መጽሐፍ ቅዱስ” ተብሎ ሲጠራ ተሰምቷል፡፡
መጠሪያቸው
እንደሚያስረዳው እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት ቀደም ሲል ከቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር ውጪ እንዲሆኑና በአዋልድነት እንዲጠሩ ያደረጋቸው
አያሌ ታዋቂ ምክንያቶች መኖራቸው ግልጽ ነው ምክንያቶቹ ከአዋልድ መጻሕፍቱ ጋር ታትመው ቢሆኑ ኑሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ባላደናገሩ
ነበር፡፡
የብሉይ
ኪዳን መምህራን ስለ እያንዳንዱ ዲዮትሮካኖኒካል መጽሐፍ በማስረጃ የተደገፈ ማብራሪያ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እስከዚያው
ድረስ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማሙባቸውን ነጥቦች በመጠቈም ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡
መጽሐፈ ባሮክ
በ1980 ዓ.ም. በታተመው የዐማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ከቀኖና መጻሕፍት አንዱ ሆኖ የቀረበው “መጽሐፈ ባሮክ” ከግእዙና ከእንግሊዝኛው ትርጉሞች የተለየ ነው፡፡ ለዐማርኛው መጽሐፈ
ባሮክ በምንጭነት ያገለገለው፥ በየትኛው ቋንቋና በምን ዘመን የታተመው መጽሐፍ እንደ ሆነ ስላልተጠቀሰ
ከምንጩ ጋር እንዲመሳከር ለማድረግ አላመቸም፤ ስሕተቱ ከምንጩ ወይም ከዐማርኛው ትርጉም እንደሆነም አልታወቀም፡፡ ሆኖም አንባቢ
እንዲያነበውና የራሱን ፍርድ እንዲሰጥ ልዩነት ከታየባቸው ቍጥሮች ዐሥሩ ለዐይነት በዐማርኛ፥ በግእዝና በእንግሊዝኛ ቀርበዋል፡፡
1. ዐማርኛው
መጽሐፈ ባሮክ በ1980 ዓ..ም በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የታተመ ነው፡፡
2. ግእዙ
መጽሐፈ ባሮክ በኤርትራ፥ በኢትዮጵያ፥ በፓሪስ፥ በሎንዶን፥ ተከማችተው ከሚገኙት ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ጋር በማመሳከርና በማስማማት
ተዘጋጅቶ በ1918 ዓ.ም. አሥመራ በማኅተመ ፍራንችስካና የታተመ ነው፡፡
3. እንግሊዝኛው
መጽሐፈ ባሮክ እ.ኤ.አ. በ1985 በኦክስፎርድ የታተመው ዘኒው ጀሩሳሌም ባይብል ነው፡፡
ዐማርኛው
|
ግእዙ
|
እንግሊዝኛው
|
ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮአቄም ልጅ ከኢኮንያን
የተጻፈውን ከሕዝቡም ዘንድ ወደ እርሱ የመጣውን
|
ወአንበበ ባሮክ ዘ መጽሐፈ በእዝነ ኢኮንያስ ወልደ ኢዮአቄም ንጉሠ ይሁዳ ወበእዝነ ኵሉ ሕዝብ ዘመጽአ ኀበ መጽሐፍ
|
Baruch
read the text of this book aloud to Jeconiah son of Jehiakim, king of Judah,
and to all the people who had come to hear the reading.
|
የባቢሎን ሰዎች የእግዚአብሔር ማደሪያ ንዋየ ቅድሳቱን ከቤተ መቅደስ በወሰዱ ጊዜ በኢየሩሳሌም ወዳሉ ካህናት
የላከውንም ይህንን መጽሐፍ ባሮክ አነበበ
|
ወበእዝነ ኀያላን ወደቂቀ ነገሥት ወበእዝነ
ሊቃናት ወበእዝነ ሕዝብ እምዐቢይ እስከ ንኡስ ኵሎሙ እለ የኀድሩ ባቢሎን መልዕልተ ፈለገ ሶዲ
|
To
the nobles and the sons of the king, and to the elders, to the whole people,
that is, to the least no less than to the greatest, to all who lived in
Babylon beside the river Sub.
|
ናቡከደነፆር ኢኮንያንን ከማረከው በኋላ የኢየሩሳሌምንም ወገኖች ከማረካቸው በኋላ ወደ ባቢሎንም ከወሰዳቸው
በኋላ ሴዴቅያስ የብሩን ዕቃ አሠርቶ ከወርቁ ጋር ሰደደላቸው፡፡
|
ወበከዩ ወጾሙ ወጸለዩ በቅድመ እግዚአብሔር
|
On
hearing it they wept, fasted and prayed before the Lord.
|
ዘመናቸው ጠፈር በአድማስ ጸንቶ የኖረውን ያህል ጸንቶ ይኖር ዘንድ ስለ ባቢሎን ንጉሥ ስለ ናቡከደነፆር
ድኅነት ስለ ልጁ ስለ ብልጣሶር ደኅነት ለምኑ አለ፡፡
|
ወአስተጋብኡ ብራሬ ብእሲ ብእሲ በከመ ክሂሎቱ
|
And
they collected as much money as each could afford
|
ፈጣሪያችን እግዚአብሔርን በድለናልና ለኛም ወደ ፈጣሪችን ወደ እግዚአብሔር ለምኑልን አለ
|
ወፈነውዎ ኢየሩሳሌም ኀበ ኢዮአቄም ወልደ ሕልቅያ ወልደ ሱሉም ካህን ወኀበ ካህናት ወኀበ ኵሉ ሕዝብ ዘሀለዉ
ምስሌሁ ኢየሩሳሌም
|
And
sent it to Jerusalem to the priest Jehoiakim son of Hilkiah. Son of Shallum,
and the other priests, and all the people who were with him in Jeruslaum.
|
ካህናቱ ቀድሞ ደግሞ ሕግን በበዓል ቀን ያነቧት እንደነበረ ያችንም መጽሐፍ በእግዚአብሔር ማደሪያ በቤተ
መቅደስ አንብቧት አለ፡፡
|
አመ ነሥኡ ንዋየ ቤተ እግዚአብሔር ዘተሀየደ እም ቤተ መቅደስ ከመ ይሚጥዎ ኀበ ምድረ ይሁዳ በዐሥሩ ለወርኀ
ሲባን ለንዋይ ዘብሩር ዘገብረ ሴዴቅያስ ወልደ ኢዮስያስ ንጉሠ ይሁዳ
|
Also
on the tenth day of sivan he was given the utensils of the house of the Lord,
which had been removed from the temple, to take them back to the land of
Judah; these were silver utensils which Zedekia son of Josiah king of Judah,
had had made.
|
የፈጣሪችን እግዚአብሔርን ቸርነት ተናገሩ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሰዎች የኛን ፊት ኀፍረት ሸፈነን የመሳፍንቱና
የነገሥታቱን ፊት የመምራኑንና የካህናቱን ፊት ኀፍረት ሸፈነው፡፡
|
እምድኅረ ነሥኦሙ ናቡከደናፆር ንጉሠ ባቢሎን ለኢኮንያስ ወለመኳንንት ወለፂዉዋን ወለከሃልያን ወለሕዝበ ምድር
እም ኢየሩሳሌም ወወሰዶሙ ባቢሎን፡፡
|
After
Nebuchadenzaar king of Babylon had
deported Jeconiah from Jerusalem to Babylon together with the princes, the
metal workers, the nobles and the common people.
|
የፈጣሪያችን የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰማንም በሠራልን በፈጣሪያችን በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ጸንተን አልኖርንም
|
ወይቤሉ ናሁ ፈነውነ ለክሙ ብሩረ ወቦቱ ተሣየጡ ለመሥዋዕት በእንተ ኀጢአት ወዕጣነሂ ወግበሩ መና ወአዕርጉ
በምሥዋዐ እግዚአብሔር አምላክነ
|
Now
they wrote, we are sending you money to pay for burnt offerings, offerings
for sin and incense. Prepare oblations and offer them on the altar of the
Lord our God;
|
አባቶቻችንን ከግብጽ አገር ካወጣቸው ጀምሮ እስከዚች ቀንድ ደረስ ፈጠሪያችን እግዚአብሔርን ወነጀልነው
|
ወጸልዩ በእንተ ሕይወተ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን ወበእንተ ብልጣሶር ወልዱ ከመ ይኩን መዋዕሊሆሙ ከመ
መዋዕለ ሰማይ ዲበ ምድር
|
And
pray for the long life of Nebucanddenzzar king of Babylon, and of his son
Belshaazar, that they may endure on earth as long as the heavens endure;
|
ሄደን ለአሕዛብ ጣዖቶች ተገዝተናልና በሙሴም ኦሪት የተጻፈው መከራ ደርሶብናልና ይህ ጽኑ እርግማን አገኘን
አለ፡፡
|
ወየሀበነ እግዚአብሔር ኀይለ ወያብርህ አዕይንተነ ወንሕየው በታሕተ ጽላሎቱ ለናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን
ወበታሕተ ጽላሎቱ ለብልጣሶር ወልዱ ወከመ ንትቀነይ ሎሙ ለብዙኅ መዋዕል ወከመ ንርከብ ሞገስ በቅድመ ገጾሙ
|
And
that the Lord may give us strength and enlighten our eyes, to that we may
lead our lives under the protection of Nebuchadenezzar king of Babylon and of
his son beleshazar. And that we may serve them for along time and win their
favour.
|
ገና ከመነሻው ጀምሮ ያለውን ልዩነት ለማሳየት ከምዕራፍ 1 ቍጥር 3 ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ 10 ቍጥሮች በዚህ ለማቅረብ ተሞከረ እንጂ የልዩነቱ
ዓይነትና መጠን ብዙ ነው፡ ለምሳሌ በአንዳንድ ቦታ የቍጥር መለዋወጥም አለ፡፡ ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ምዕራፍ ከግእዙና ከእንግሊዝኛው
ባሮክ በቍጥር ያንሳል፡፡
1ኛው ምዕራፍ 12
ቍጥሮች 22 ቍጥሮች 22 ቍጥሮች
2ኛው ምዕራፍ 17
ቍጥሮች 35 ቍጥሮች 35 ቍጥሮች
3ኛው ምዕራፍ 31
ቍጥሮች 38 ቍጥሮች 38 ቍጥሮች
4ኛው ምዕራፍ 15
ቍጥሮች 37 ቍጥሮች 37 ቍጥሮች
5ኛው ምዕራፍ 8 ቍጥሮች 9 ቁጥሮች 9 ቁጥሮች
በድምሩ 83 141 141 ይዘዋል፡፡
ግእዙና እንግሊዝኛው መጽሐፈ ባሮክ ያሰፈሩት ሐሳብ በዐማርኛው መጽሐፈ
ባሮክ ስላልተካተተ ዐማርኛውን መጽሐፈ ባሮክ በ58 ቍጥሮች ጐዶሎ አድርጎታል፡፡ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ቃል ስላይደለ ቢጐድልም
ቢተርፍም ላያስደንቅ ይችላል፡፡
ይቀጥላል
በጮራ ቍጥር 7 ላይ የቀረበ
No comments:
Post a Comment